የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት አገልግሎትን በማቀላጠፍ አርዓያነት ያለው ተግባር እየሰራ ነው!" - ዶ/ር አለሙ ስሜ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማችን ያለውን የትራንስፖርት ችግር የሚያቃልሉ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በመንግስት እና ግል አጋርነት ወደ አገልግሎት ባስገባበት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ መልዕክት አስተላልፈዋል::