የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ያለበትን ደረጃ ለማየት የስራ ጉብኝት ማድረጉ ተገለፀ።
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ያለበትን ደረጃ ለማየት የስራ ጉብኝት ማድረጉ ተገለፀ።
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ያለበትን ደረጃ ለማየት በዛሬው ዕለት ከዋና ማዕከሉ ወይም ከለቡ ጣቢያ በመጀመር እስከ አዳማ ጣቢያ ድረስ ከተሳፋሪዎች ጋር በባቡር በመጓዝ ለማየት ተችሏል።
በዚህ የስራ ጉብኝት ላይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስተር ዴዕታ የተከበሩ አቶ በረኦ ሀሠን በረኦ በስፍራው በመገኘት እንደገለፁት በጉዟቸው የተገልጋይ ማህበረሰብ ጥያቄዎችን፣ የተርሚናሎች የውስጥ ፅዳትና አደረጃጀትን፣ በመስመሩ ለይ ያሉ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራሮችንና በተለይ ከባቡር እስከ ደጃፍ የሚሰጠው የለስት ማይል ትራንስፖርት በአደማና ለቡ ጣቢያዎች ላይ ተጠናክሮ የሚሄድበትን ሁኔታዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እና ምልከታዎችን ማድረጋቸው አብራርተዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ባቡር የሁሉም ለሁሉም የሆነ ውድ ሀብታችን በተለይ በወጪ ገቢ ጭነትና የህዝብ ትራንስፖርትን አስተማማኝ፣ ተደራሽ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለምነውን ሀገራዊ ውጥናችንን የምናሳከበት ትልቁ ሀብታችን ነው። ስለሆነም ሁለንተናዊ ትኩረታችንን ለባቡራችን መስጠት እንደሚገባ አያይዘው ገልፀዋል።