የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ከፍተኛ ኃላፊዎች “የኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ 2024” ኤግዚቪሽንን ጎበኙ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዴንጌ ቦሩ በተገኙበት ኤግዚቪቪኑን የጎበኙት የመምሪያው ኃላፊዎች በአረንጓዴ ትራንስፖርት ላይ የሚሰሩ ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ተቋማት ያቀረቧቸውን ምርትና አገልግሎቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን የሚያመርቱ፣ የሚገጣጥሙና ወደ አገር ውስጥ አምጥተው የሚሸጡ ተቋማት ምርቶቻቸውን በኤግዚቪሽኑ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2014 ኤግዚቪሽን ዛሬ 4ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን እስከ ህዳር 20/2017 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Share this Post