የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች የፀረ ሙስና ቀንን አከበሩ

በውይይት መድረኩ ላይ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ሙስና በሀገር ሁለንተናዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ሁላችንም በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል ብለዋል፡፡

የሙስናን ውስብስብነት በመረዳት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ትግል ማድረግ ይገባል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ህዝብን እንድናገለግልበት የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ከሌብነት የጸዳ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅብናል ሲሉ አክለዋል፡፡

በተጨማሪም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ አገልግሎቶች ለሙስና ያላቸውን ተጋላጭነት ለመቀነስ የዲጂዚታላይዜሽን አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም አመራርና ሠራተኛ ሀገሩን በታማኝነት ማገልገል አለበት ብለዋል፡፡

በመድረኩ የሙስና ወንጀል ህጎች ምንነት ላይ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በሀገርም ሆነ በተቋም ደረጃ ሙስናን በመዋጋት ከሙስና የፀዳ ተቋምና ዘርፍ ለመገንባት እያንዳንዱ አካል ስለሚኖረው ድርሻ ውይይት ተደርጓል፡፡

Share this Post