የሎጂስቲክስ ዘርፍ ተቋማት ውጤታማ ስራ እየሰሩ እንደሆኑ ተገለፀ
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት በኢፌዲሪ 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ስብሰባ በመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
በማብራሪያቸው እንደገለፁትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር፣ ቁጥር በመዳረሻ ብዛት፣ አዳዲስ አየር ማረፊያዎችን አስመርቆ ስራ በማስጀመር፣ የበረራ ምልልስን በመጨመር እድገት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አየር መንገዱ በሰራቸው ስራዎች ልክም ትርፋማነቱ ጨምሯል ብለዋል፡፡
በተለይ በቅርቡ በአፍሪካ ትልቁን አየር ማረፊያ ለመገንባት ጥረት መጀመሩን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ባለው ሂደትም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ በማብራሪያቸው አንስተዋል፡፡
በሚቀጥሉት አምስት ወይም ስድስት ወራት አብዛኛው የአዲሱ አየር ማረፊያ የዲዛይንና የፋይናንስ ጉዳይ ከተጠናቀቀ ስራው እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡ ይህ አየር ማረፊያ ትልቅ ሀገራዊ ስትራቴጂክ ፐሮጀክት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስክስ አገልግሎትም ተጨማሪ መርከቦችን እየጨመረ ስራውን ለማዘመንና ትርፋማነቱን ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የማጓጓዝ አቅም አምና ከነበረው በእጅጉ እያደገ መጥቷል ሲሉ በማብራሪያቸው አንስተዋል፡፡