የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የአውቶቡስ ማቆሚያ ተርሚናል ግንባታዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የአውቶቡስ  ማቆሚያ ተርሚናል ግንባታዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡
መጋቢት 12/2017 ዓ.ም (ትሎሚ) ፡- ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የአውቶቡስ ማቆሚያ ተርሚናል ግንባታዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ  ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች እና ከፕሮጀክቶቹ አማካሪዎች ጋር በመሆን ጉለሌ እና ጀሞ አካባቢ  በግንባታ ላይ ያሉ አውቶብስ ተርሚናሎች የመስክ ጉብኚት አድርገዋል፡፡
በመስክ ምልከታው ወቅት የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የአውቶቡስ  ማቆሚያ ቦታ ችግር የሚቀርፉ ተርሚናሎች ግንባታ በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ስለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ግንባታዎቹ ሲጠናቀቁ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የአውቶቡስ  ማቆሚያ ቦታ ችግር ከመቅረፉም ባሻገር  አውቶብሶቹ አሁን እየቆሙበት ያለው ቦታ ስለሚለቀቅ ለከተማው የተሽከርካሪ ማቆሚያ እጥረት እንዲቀንስ አስተዋፅኦ እንዳለው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የምዕራብ ቅርንጫፍ ስራ አስከያጅ አቶ ልዑል ሀይሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ልዑል በግንባታ ላይ ያሉት አራቱ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የአውቶቡስ  ማቆሚያዎች የካ አካባቢ የሚገኘው የምስራቅ ተርሚናል፣ ጀሞ የሚገኘው የምዕራብ ተርሚናል፣ ጉለሌ የሚገኘው የሰሜን ቅርንጫፍ ተርሚናል እና አቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው የደቡብ ተርሚናሎች መሆናቸውን ጠቁመዋል ፡፡
ሁሉም ፕሮጀክቶች የምድረ ግቢ የአስፋልት ስራ፣ የተሸከርካሪዎች የእጥበት አገልግሎት፣ የጋራዥ ፣ የአውቶብሶች ማቆሚያ ፣ የንግድ ሱቆች፣ የመሰብሰቢያ አደራሾች ፣የሰራተኞች ቢሮ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች አገልግሎቶች የሚሰጡበትን የሚያካትቱ ግንባታዎች መሆናቸውን  አቶ ልዑል አስረድተዋል፡፡
ተርሚናሎቹ ለመንግሰት ሰራተኞች እና ለከተማው ህብረተሰብ እየተሰጠ ያለውን የትራንስፖርት  አገልግሎት እንዲሻሻል እንደሚያደርግም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን የመስክ ምልከታውን በተመለከተ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች እና ከፕሮጀክቶቹ አማካሪዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ  በሁሉም ተርሚናሎች የሚቀሩት የማስተካከያ እና የእርማት ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ  አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Share this Post