ወደሀገር ውስጥ የገቡ ዘጠና ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ስራ ጀመሩ
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የማሽነሪ ፍላጎት እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ ከተፈጠረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ከተፈጠረው የነዳጅ እጥረት ለመቋቋም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል።
እነዚህ ተሽከርካሪዎች የቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ግንባታ 24/7 ግንባታው እንዲከናወን በኮንትራክተሩ አማካኝነት የተገዙ መሆኑ ተገልጿል።
ከባድ ጭነት ገልባጭ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎቹ በጥራታቸው እና ለኮንስትራክሽን ስራ በጉልበታቸውም ሆነ ጭነት የማንሳት አቅማቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
እነዚህ ተሽከርካሪዎች በሀገራችን ከሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ጋር ተያይዞ በጥናት የተለዩ የደህንነት ችግሮችን የሚቀርፉና የጥራት መለኪያዎችን የሚያሟሉ፤ የተፈቀደላቸውን የጭነት መጠን ብቻ የሚጭኑ፤ አራት መቶ ኪሎዋት የባትሪ አቅም ያላቸው እንዲሁም አነስተኛ ድምፅ ያላቸው እንዲሁም ከመንገድ ደህንነት አኳያ የፍጥነት ገደብ የተቀመጠላቸው በመሆናቸው የአረንጓዴ ትራንስፖርት ስትራቴጂን ሙሉ በሙሉ ያሟሉ መሆናቸውን ሚኒስትር ደኤታው አክለው ገልፀዋል ተገልጿል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲስፋፋ ከፍተኛ የሆነ ርብርብ እየተደረገ መሆኑና እነዚህ ተሽከርካሪዎች እና ቻርጅ ማድረጊያ ማሽኖች ከቀረጥ ነፃ የገቡ መሆናቸውን ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል።
መንግስት በሚሰጠው የውሳኔ ሰጭነት እና ማበረታቻ ማዕቀፎች በመታገዝ ሀገር ውስጥ 17 የሚሆኑ ከሁለት እግር እስከ አራት መቶ ኩንታል የመጫን አቅም ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገጣጣሚ ተቋማት ማፍራት መቻሉን ሚኒስትር ደኤታው ጨምረው ገልጸዋል።