ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ በአየር ትራንስፖርት እና በአቪዬሽን ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፁ።

የሞዛምቢክ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ፀሐፊ ቻንጉን ማቦቴ ከኢትዮጵያ ሲቨል አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር በተደረገው ስምምነት መደሰታቸውን የገለፁ ሲሆን ተግባራዊ እንዲሆን ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

ሚኒስትር ደኤታው አቶ በርኦ ሀሰን የአቪዬሽን ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ተወዳዳሪ ያለበት ዘርፍ በመሆኑ ውጤታማ ለመሆን እና ከባቢያዊ እና አህጉራዊ ትስስር ለመፍጠር ከሞዛምቢክ ጋር የተደረገው ስምምነት ትልቅ ድርሻ ያለው ነው ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትር ደኤታው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ተግባራዊ ለማድረግ የአየር ትራንስፖርት ተደራሽነት ለማሳደግ እና የተደረጉ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጅነት ተናግረዋል።

Share this Post