"ሐምሳ በመቶ የሚሆኑት የአፍሪካ አገራት ዜጎች የኤሌክትሪክ ሃይል እና የንፁህ ዉሃ አቅርቦት እጥረት አለባቸው" ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ( የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስትር)
ክቡር ሚኒስትሩ ይሄንን ያሉት በመካሄድ ላይ በሚገኘው የበኢትዮጵያ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ያለው ስምተኛው ( የPIDA WEEK) መርሃ-ግብር የመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት ነው።
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም የኤሌክትሪክ ሃይል እና ንፁ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ አፍሪካዊያን ትብብርንና ቅንጂትን በማላቅ ለመጪው ትውልድ የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ይኖርብናል ብለዋል።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የኮሪደር ልማት፣የህዳሴ ግድብ የሃይል አቅርቦት፣ የኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር እና የኢትዮጽያ አየር መንገድ የላቀ አገልግሎትን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ብክለት ተፅእኖን ለመቀነስ የአረንጓዴ አሻራ እና የአረንጓዴ ትራንስፖርት በትኩረት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።
የአየር ለውጥ አደጋን ለመቋቋም አካታች የመሰረተ ልማት ግንባታ እና ለአየር ንብረት የማይበገር የመሰረተ ልማት ግንባታ ተደራሽ ለማድረግ የቀጠናዊ ትብብር ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል