የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
ሚኒስትር ዴኤታዋ ይህን ያሉት የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች የኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ 2024 ኤግዚቪሽንን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት እንደሀገር በተያዘው የ10 ዓመት ልማት እቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል አረንጓዴ ትራንስፖርትን በማስፋፋት የበካይ ጋዝ ልቀትን መቀነስ አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ይህን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ጥቅም ላይ በማዋል የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ እየሰራ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ ተቋማት ተቀናጅተው በመስራት ካለን አረንጓዴ የኃይል ምንጭ አንፃር በስፋት በመጠቀም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን እንደ ሀገር መቀነስ ይገባል ሲሉ አክለዋል፡፡
በተጨማሪም አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት የሚያግዙ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራዎችን ከመስራት በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቻርጅ መሙያ መሠረተ ልማቶች፣ የጥገናና የመለዋወጫ አገልግሎቶች እንዲሟሉ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡