በኤሌክትሪካ ተሽከርካሪ ማስፋፊያ ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ ከባለድረሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ
ዘላቂ እና ለአካባቢ ምቹ የሆነ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋት ተቋሙ በትኩረት ከያዛቸው አሰራሮች አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና መሰረተ ልማት እንዲሰፋፋ ለማደረግ በመሆኑ የባለድርሻ አካላትተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ደኤታው አቶ በርኦ ሀስን ተናግረዋል።
የኤሌክትሪካ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ እና እንዲስፋፋ የተለያዩ የማበረታቻ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ደኤታው በውይይቱ ላይ ተናግረዋል ::
የኤሌክትሪካ ተሽከርካሪዎች ማምረት ላይ ለሚሰማሩ የሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በረቂቅ ስትራቴጂው ውይይት ላይ ተገልጿል፡፡
በረቂቅ ስትራቴጂው ላይ አስተያያት እና ጥያቄ ከባለድርሻ አካላት በኩል የተነሳ ሲሆን የተነሱ አስተያየቶች እንደ ግብዓት ተወስዶ በአጭር ጊዜ ስትራቴጂው ፀድቆ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡