በስነ ምግባራዊ አመራር እና ተቋማዊ ስኬት ላይ ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በስነ ምግባራዊ አመራር እና ተቋማዊ ስኬት ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

በስለጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ሙስናን አስቀድሞ ለመከላከል በሰዎች የባህሪ ለውጥ እና ግንዛቤ መፍጠር ስለሚያስፈልግ እንዲህ ያለ ስልጠና አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ማህበራዊ እሴት የሆኑትን ሀይማኖት እና ባህል ሙስናን ለመከላከል ጉልህ ሚና ስላላቸው እነዚህን እሴቶች ማጉላትእንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር አለሙ ሙስና እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ተቋም መኖሩን ገልፀው በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሌብነት የማይመች አደረጃጀት የመፍጠር ኃላፊነት አለብን ብለው ሀገርን እና ህዝብን የሚጎዳ ተግባር የሚፈፅም አካል ሲኖር ጠበቅ ያለ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በዘርፉ ላይ ያለውን ብልሹ አሰራር ለመከላከል የተጀመሩ እና በሂደት ላይ ያሉ የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ አሰራሮች አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል፡፡

Share this Post