የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ከማስፋፋት አንጻር በኤሌክትሪክ እና ታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችንና ተያያዥ ግብአቶች ለሀገራችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ፣ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ኢትዮ ግሪን ሞቢሊቲ 2024 አዉደርዕይና ሲምፖዚየም እያዘጋጀ ይገኛል፡፡

በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር የሚያደርጉ አካላት ጥቅሞች፤ የስፖንሰር አድራጊ ድርጅት ሎጎ በሑነቱ የህትመት ውጤቶች ላይ ይታተማል፡፡ በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ የሚዲያ ሽፋን የማግኘት፣በፕሮግራሙ ማስታወቂያ ቦታ ማግኘት፣በሚካሄዱ መድረኮች የቪአይፒ መቀመጫ የማግኘት እና ፣በሌሎች የተጓዳኝ ሑነቶች ላይ የሚሳተፉበት የመግቢያ ቲኬት የሚያገኙ ይሆናል፡፡

በወርቅ ደረጃ ስፖንሰር የሚያደርጉ ድርጅቶች በበኩላቸው፤ ለሑነቱ በሚዘጋጁ የህትመት ውጤቶችና በአዘጋጁ በድረ-ገጽ ላይ የመተዋወቅ እድል፣ በሚካሄዱ ጋዜጣዊ መግለጫዎች እና የሚዲያ ሽፋን ላይ የመተዋወቅ፣ የድርጅታቸው ሎጎ በሑነቱ የህትመት ውጤቶች እና በድረ-ገጽ መተዋወቅ፣ ለሑነቱ ተዘጋጅተዉ በሚለቀቁ ፕሬስ ሪሊዝ ላይ እና የሚዲያ ሽፋን የማግኘት እና ሌሎች የተጓዳኝ ሑነቶች ላይ የሚሳተፉበት የመግቢያ ቲኬት ያገኛሉ፡፡

የብር ደረጃ ስፖነሰር የሚያደርጉት ድርጅቶች፤የድርጅታቸው ሎጎ በሑነቱ የህትመት ውጤቶች እና በድረ-ገጽ የመተዋወቅ፣ ለሑነቱ ተዘጋጅቶ በሚለቀቁ ፕሬስ ሪሊዝ ላይ የድርጅቶ ስም ዝርዝር ውስጥ የመካተት፣ የድርጅታቸው ሎጎ በሑነቱ የህትመት ውጤቶች ሩብ ገፅ ላይ የመተዋወቅ፣ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ የመተዋወቅ እና በሌሎች የተጓዳኝ ሑነቶች ላይ የሚሳተፉበት የመግቢያ ቲኬት ያገኛሉ፡፡

የመዳብ ደረጃ ስፖንሰር የሚያደርጉት ድርጅቶች፤ የድርጅታቸው ሎጎ በሑነቱ የህትመት ውጤቶች እና በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ ተደራሽ የመሆን፣ በሑነቱ መርሃግብር ትውውቅ ዝርዝር ውስጥ የመካተት፣ በሁሉም የተቋሙ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የመተዋወቅ እድል የማግነት እና፣ በሌሎች የተጓዳኝ ሑነቶች ላይ የሚሳተፉበት የመግቢያ ቲኬት ጥቅሞች የሚያገኙ ይሆናል፡፡

Share this Post