የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የ8ኛው የአፍሪካ መሠረተ ልማት ኢነርጂና ICT ማስፋፍያ /PIDA Week/ ከፈቱ
8ኛው የአፍሪካ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ሳምንት "ለአፍሪካ ዘላቂ ዕድገት ችግሮችን የሚቋቋም አካታች መሠረተ ልማትን ማጎልበት" በሚል መር ሀሳብ በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ በይፋ ተከፍቷል ።
የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ፒዳ) አጀንዳ 2063 እንዲሳካ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
በአፍሪካ ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር እና የንግድ ግንኙነትን በማጎልበት ዘላቂ ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚያስችል መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ምዕራፍ 1 እና ምዕራፍ 2 ፕሮጀክቶችን ታሳቢ ያደረጉ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን መስራቷንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ በተለይ በመንገድ እና በባቡር መሠረተ ልማት ግንባታ እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ዙሪያ የሰራቻቸው ስራዎች የሀገሪቱን መልክ እና ዕድገት እየቀየሩ ስለመሆናቸውም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል