መንግስት ለማዳበሪያ 84 ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ እንደሚያደርግ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተናገሩ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ መንግሰት ለግብረናው በሰጠው ትኩረት በአንድ ኩንታል ከ3,700 ብር በላይድጎማ ያደርግል ብለዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዳበሪያ ዋጋ ጋር ተያይዞ ማዳበሪያ ሀገሪቱ ከውጭ ስለሚገባ የማደበሪያ ዋጋ በውጭ ሀገራት የሚወስን ነው ብለዋል፡፡

ማዳበሪያ ከውጭ መግዛት ብቻ ሳይሆን በየቀኑ ከወደብ 150 ሺ ኩንታል በላይ ማደበሪያ በማንሳት የፀጥታ ችግር በአለባቸው የሀገሪቱ ክልሎች በመከላከያ በማጀብ ወደ አርሶ አደሩ እያደረስን ነው ብለዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ሀገር ውስጥ በዘላቂነት ማዳበሪያ ለማምረት በተደረገው ጥናት 2.5 እስከ 3 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልፀው፡ በቀጣይ የሀገሪቱን የማደበሪያ ፍላጎት ለሟሟላት በመንግሰትም ሆነ በግሉ ሴክተር ትብብር በቀጣይ ለማምረት እቅድ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

Share this Post