ላለፉት አራት ቀናት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የአፍሪካ መሠረተ ልማት ፕሮግራም (PIDA WEEK) መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ።
በንግግራቸውም እንደ አፍሪካ የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚያገለግሉ መሆን አለበት ብለዋል።
አክለውም አቅማችንን አቀናጅተን እና ተባብረን አካታች የመሠረተ ልማት ተደራሽ በማድረግ የአፍሪካን ብልፅግና እውን እናድርግ ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ሚኒስትሩ የአፍሪካ መሠረተ ልማት ፕሮግራም (PIDA WEEK) መርሃ-ግብር ተሳታፊዎች የአዲስ አባበን የኮሪደር ልማት ፣ አደዋ ሙዚዬም እና በነገው እለት የሚጠናቀቀውን የኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ 2024 አውደ ርዕይና ሲምፖዚዬም እንድጎበኙ ጥሪአቸውን አስተላልፈዋል።
የአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ (AUDA-NEPAD) ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ናርዶስ በቀለ በበኩላቸው የአፍሪካ መሠረተ ልማት ፕሮግራም (PIDA WEEK) መርሃ -ግብር ስኬታማ እንዲሆን የኢትዮጽያ መንግስትም ለተጫወተው ሚና የላቀ እንደነበር በማንሳት ምስጋና አቅርበዋል።