በቡሌ ሆራ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው
በቡሌ ሆራ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) በኦሮሚያ ክልል ቡሌ ሆራ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በውይይት መድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር እየመከሩ ነው፡፡
መድረኩ" ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና "በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በማርታ ጌታቸውና ለሊሴ ተስፋ