የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀይ ባህርን እና ሌሎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በሚመለከት ለጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ ዶ/ር ካቀረቧቸው መካከል፡-
የቀይ ባህርን ጥያቄ ይበልጥ ወደ ፊት ለመግፋት መንግሰት በቀጣይ 5 ዓመታት ምን አይነት የዲፕሎማሲ አቅጣጫን ይከተላል?
ታሪካዊ የባህር በር ጥያቄን ለማዛባት እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ባእዳን እና ባንዳን ለማስታገስ ምን አይነት እርምጃ ይወሰዳል?
በኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝብ ጥያቄን ለመፍታት እና የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ የሚደነቅ ነው።በኢትዮጵያ ዘላቂ የሰላም ግንባታን ከማጠናከር አንጻር ምን አቅጣጫ ተይዟል ?
በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማቃለል መንግስት የያዘው አቅጣጫ ካለ ቢብራራ
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ። የሀገርን ሰላም አና አንድነት ለማናጋት በባንዳነት ተግባራት ላይ የተሰለፉ አካላትን እንቅስቃሴ መንግስት እንዴት ይመለከታል ?
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ ለህዝብ የሚኖራቸው ፋይዳ ከፍተኛ ቢሆንም ከአካባቢው ለልማት የሚነሱ ዜጎች ጉዳይ እንዴት ይታያል ?
መንግስት የከተማ ልማትን ለማሳደግ እየሰራቸው የሚገኙ ተግባራት ለሀገር ብልጽግና ከሚኖራቸው ፋይዳ ባሻገር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው
የወጣቶች ስራ አጥነትን ጉዳይ በዘላቂነት ትኩረት ለመፍታት ምን ተይዟል?
በከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ችግር ለማስተካከል የሚደረገውን ጥረት አስመልክቶ ማብራሪያ ቢሰጥ