ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ሥራ ቢኖርም ሰራተኛ ማግኘት በጣም ከባድ ሆኗል - ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ሥራ ቢኖርም ሰራተኛ ማግኘት በጣም ከባድ ሆኗል አሉ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፥ ወላጆች ከከተማ ውጪ የሚሰሩ ሥራዎችን ወጣቶች እንዲሞክሯቸው ማበረታታት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ለአብነትም ‎በግንባታ ላይ በሚገኘው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቂ የሰው ኃይል ማግኘት አዳጋች መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የቤት ሰራተኝነት ሥራን የሚሰሩ ሰዎች ቁጥር እጅግ ጥቂት መሆኑን ጠቁመው፥ ለተመሳሳይ ሥራ ከሀገር የሚወጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

‎ከሀገር የወጡ ወጣቶች በቀን ለ16 ሰዓታት ያህል ሰርተው ራሳቸውን ሲለውጡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ወጣቶች ግን ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም ክፍተት እንዳለባቸው ነው የገለጹት፡፡

‎

‎በሁለት እና ሶስት የሥራ ፈረቃዎች በመስራት አቅምን ማሳደግና መተጋገዝ ካልተቻለ የኑሮ ውድነት ከዚህ በላይ ሊሆን አንደሚችል አመልክተዋል፡፡

Share this Post