ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ በርኦ ሀሰን የኢትዮ ጅቡቲ የመንገደኞች ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ተመለከቱ

ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ በርኦ ሀሰን የኢትዮ ጅቡቲ የመንገደኞች ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ተመለከቱ

የካቲት 8/2016 ዓ.ም (ትሎሚ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ በርኦ ሀሰን የኢትዮ ጅቡቲ የመንገደኞች ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ በሰበታ ባቡር ጣቢያ በመገኘትና ከተሳፋሪዎች ጋር በመጓዝ ምልከታ አድርገዋል፡፡

ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው በትናንተናው እለት ከሰበታ ባቡር ጣቢያ እስከ አዳማ ድረስ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ያለበትን ደረጃ በተመለከተ መንገደኞችን አነጋግረዋል፡፡

በመንገደኞች የባቡር ትራንስፖርት ላይ የተሳፋሪዎችን አያያዝ፣ የባቡር ጣቢያ እና የመሳፈሪያ ቦታዎችን ፅዳትና አደረጃጀት፣ የመስመሩን ደህንነት ለማስጠበቅ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

ተሳፋሪዎችን ባነጋገሩበት ወቅት የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የመንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ቀልጣፋና ምቹ መሆኑንና ከተሳፋሪዎችም ገንቢ አስተያቶችን መቀበላቸውን ሚኒስቴር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አስተማማኝ የሆነ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ የሀገራችንን የወጪ ገቢ ጭነት በተቀላጠፈ መንገድ በማጓጓዝ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን ክቡር አቶ በርኦ ሀሰን አመላክተዋል፡፡

All reactions:

1717

Share this Post