የአሜሪካ ኩባንያዎችን ቀልብ የሳበው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ

ከ10 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ የሚጠይቀው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የውጭ ብድርን ብቻ ከመጠበቅ ይልቅ ለአሥር ዓመታት ጥናት ሲደረግበት የቆየውንና ውጤታማነቱ የተረጋገጠውን ይህን ታላቅ ፕሮጀክት በራሱ አቅም ግንባታውን መጀመሩ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፕሮጀክቱ ስልታዊ ጠቀሜታና ተስፋ ሰጭነት የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎችን ቀልብ የሳበ ሲሆን ሰሞኑን በአሜሪካ በተካሄደው የፋይናንስ ሮድሾው መድረክ ላይ የአሜሪካ ኩባንያዎች በምህንድስና፣ በቴክኖሎጂ እና በደህንነት ዘርፎች በፕሮጀክቱ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ኢትዮጵያ ለታላላቅ ፕሮጀክቶች ያላትን ቁርጠኝነትና በራስ የመቆም አቅሟን የምታሳይበት አዲስ ምዕራፍ ሆኖ ለአፍሪካ ተምሳሌትነቷን የሚያረጋግጥ ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል ።

Share this Post