የሃይማኖት መቻቻልን በተመለከተ፦
በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚከተላቸው እምነቶች የተቀራረቡ እና የሰላም ተምሳሌቶች ለመሆናቸው፣ በታሪክም አብረው የመኖራቸው እውነታ ለዚህ ምስክር ነው። ወቅታዊ ግጭቶች የሃይማኖት ወይም የብሄር ሳይሆኑ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅምን ለመደበቅ በነውጠኞች የሚቀሰቀሱ ናቸው። በመሆኑም ሀገርን በዘላቂነት ለማጽናት ህዝቡ የጥላቻ ቅስቀሳዎችን በመመከት፣ እንደ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ያሉ የሀገር ህልውና ጠባቂ ተቋማትን በሰለጠነ መንገድ ማክበር እና መደገፍ ይገባዋል።