የፕሪቶሪያ ስምምነትን በተመለከተ፦

ከሁሉ በላይ ደግሞ አሸናፊና ተሸናፊ ወገኖች በእኩልነት ቁጭ ብለው የተወያዩበት መድረክ ነበር። መንግስት ወታደራዊ የበላይነት ከጨበጠ በኋላ የተሸነፈውን አካል በጠረጴዛ ዙሪያ አስቀምጦ መደራደርና መፈራረም ብቻ ሳይሆን፣ በችግር ውስጥ የነበሩ የታጠቁ ኃይሎችን ቀርቦ በመደገፍ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይቷል። በዚህ ስምምነት ምን ተገኘ ለሚሉ ወገኖች ቢያንስ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም መቻሉን እንደ ትልቅ ስኬት ማንሳት ይቻላል። በተጨማሪም ከ60 ሺህ ያላነሱ ታጣቂዎች የዲዲአር (DDR) ክፍያ ተፈጽሞላቸው ከሰራዊቱ እንዲቀነሱ የተደረገ ሲሆን፣ በርካታ እስረኞችና ምርከኞችም ተፈተዋል።

Share this Post