ሀገራዊ ምክክርን በተመለከተ
በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያሉትን አወንታዊ እሴቶች ይዘን እንቀጥል፤ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ነጥቦች ደግሞ ማንንም በማይጎዳ፣ የሁሉንም መብት በሚያከብርና አንድነታችንን በሚያጠናክር መልኩ እናሻሽላለን።ዋናው መገንዘብ ያለብን ነጥብ፦ አሁን የምንመክረው የአንድን ጊዜያዊ ገዥ ፓርቲ ስህተት ለማረም ብቻ አይደለም። ይልቁኑ ለዘመናት የተከማቹ ስር የሰደዱ ሀገራዊ ችግሮቻችንን በጋራ ጠረጴዛ ዙሪያ ፈትተን፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚበጅ አዲስ ማህበራዊ ውል ለመፈረም ነው። ይህ ምክክር በመወያየት፣ በመነጋገርና በመተማመን እንዴት አብሮ መኖር ይቻላል ለሚለው ታሪካዊ ጥያቄ ዘላቂ ምላሽ የምንሰጥበት ብቸኛው መንገድ ነው!”