ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር የተወሰዱ መልዕክቶች!

“የሚበጀውን መንገድ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቁ አደራ ይሆናል”

"የተሰጠን አደራ አለ። የተሰጠንን አደራ ይዘን የጀመርነውን በስኬት እናጠናቅቃለን።"

"ኢትዮጵያን አይችሏትም፤ አልቻሏትም፤ የኢትዮጵያ ነገር ትንግርት ነው"

የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ መናገሪያ ቋንቋ መሆኑን አረጋግጠናል።

"እንደ ሀገር የሚገጥመንን ፈተና መሻገር የምንችለው እንደ ወንድማማች ተያይዘን እኩል መራመድ ስንችል ብቻ ነው"

"ዘመኑ ተለውጧል፤ የቆመህ ጠብቀኝ ዘመን አልፎ በአንድ ጊዜ ብዙ ዓላማ የሚመታ ቴክኖሎጂ ላይ ደርሰናል።"

የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን መሆን ስለማይችል በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን!

"በሀገራዊ ምክክሩ ምክረ ሐሳብ መሠረት በቀጣይ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ይኖረናል"

"በሕጋዊ ምርጫ እምነት ጥለው በድምፃቸው ቅቡል መንግሥት ለማፅናት በተግባር ለታመኑ 54 ሚሊዮን ዜጎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ"

Share this Post