ጉዞ ወደ አዲስ" በሚል መሪ ቃል ከናይሮቢ ተነስተው በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች 1,600 ኪ.ሜትር በማሽከርከር አዲስ አበባ ለገቡት የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ አሊያንስ አባላት አቀበበል ተደረገ።

ከነዳጅ ጥገኝነት በመላቀቅ ታዳሽ ሃይል የሚጠቀም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍን እውን ለማድረግ መንግስት ጠንካራ የፖሊሲ ድጋፍ ስለማድረጉ አንስተዋል።

የአፍሪካ -ኢ ሞቢሊቲ አሊያንስ አባላት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ረጅም ርቀት መጓዝ አይችሉም የሚባለውን የተሳሳተ ምልከታ ያስቀረ ታሪካዊ ጉዞ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የኢትዮጵያ በአረንጓዴ ትራንስፖርት ላይ አስደናቂ ስራ እየሰራች መሆኑን መመልከት መቻላቸውን ገልፀዋል።

ጉዞው በትልቁ የምንጠብቀው የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ሳምንት አካል ሲሆን ኢትዮጵያ በኢ-ሞቢሊቲ ዘርፍ ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ በብዙሃን ትራንፖርት ፣ ባቡር ፣ ኮሪደር ልማት፣ ሀይል መሙያ ማዕከላት እንዲሁም የፖሊሲ እና ስታንዳርድ ረገድ እየሰራች ያለችውን አስደናቂ ስራ የምታቀርብበት መሆኑን ገልጸዋል።

ከኬኔያ ናይሮቢ ጀምሮ በኤሌክትራክ መኪና በተደረገው ጉዞ በአፍሪካ ኢ- ሞቢሊቲ አስተባባሪነት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፣ ፓወር ኬኒያ፣ Eazy Power plc,Munja Energy, Kabisa,የኖርዌይ ኢምባሲ፣አያት ሪኤጀንሲ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ሳምንት ከነገ ጥቅምት 4/2018 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የኢንዱስትሪ ጉብኚትን ጨምሮ በዘርፋ ልምድ ያላቸው የአፍሪካ የዘርፋ ተዋናዮች የሚሳተፋባቸው ውይይቶች እና ሌሎች ፕሮግራሞችን አካቶ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ECA) ይካሄዳል።

Share this Post