ክቡር ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ባደረጉት ንግግር ላይ የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች፡-

ሰላም ለኢትዮዽያ ዕድገት እና ግስጋሴ ያጤነና ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ህብረትን ትብብርን ለኢትዮዽያ የሚያስቀድም ተግባር የሚከናወን ይሆናል፡፡

ጥራትን መስረት ያደረገ ሁለተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል፡፡

ትምህርት፣ ጤና፣ ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት ዜጋን ማዕከል ያደረገ ልማት ይፋጠናል፡፡

ለእድገት ቁልፍ ሚና ያለቸው የኢንደስትሪ እና የግብርና ግብሃቶች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ በአቅማችን እራሱን እንዲችል ይደረጋል፡፡

የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈፃፀም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይሰራል፡፡

የታክስ መሰረትን በማዘመን ዕዳን ወግ ባለው መልኩ በማስተዳደር የመንግስት ገቢ እና ወጪ በአግባቡ የማስተዳደር አቅም እንዲያድግ ይደረጋል ፡፡

በፌዴራል መንግስት እና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈፃፀም ሁነት የተባበረ የተደጋገፈ ቀልጣፋና እንከን አልባ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

የኢትዮዽያ የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሻገር ወዳጆችን የማበራከት፣ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር እና ለቀጠናዊ ሰላም እኮኖሚዊ ትስስር ምንግዜም ቅድሚያ የሚሰጥ ተነሳሽነቶች ያሉት እና አለም አቀፍ ተቀባይነታችን የሚያሳድግ ይሆናል፡፡

የሀገራችን የኤልክትሪክ ተደራሽነት 65 በመቶ የሚያድግ ሆናል፡፡

የውሃ ተጠቃሚነት በስፋት እንዲዳረስ ደረጋል።

የጤና መድን ሽፋን ወደ 85 በመቶ እንዲድግ ይሆናል፡፡

የደን ሽፋን አሁን ካለበት 26 በመቶ እንዲድግ ደረጋል፡፡

የመሶብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲበራከቱና ከፍ እንዲሉ ይደረጋል።

የተማሪዎች ምገባ ሽፋን 70 በመቶ እንዲድግ ይደረጋል፡፡

የሀገራችን የፍትህ ዘርፍ የበለጠ የበለጠ እንዲዘምን እና የሀገራዊ የምክክር ሀሳቦች ወደ ትግበራ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

አጠቃላይ የታክስ ገቢ ወደ 9.2 በመቶ ከፍ እንዲል እና የዋጋ ግሽፈት ወደ ነጠላ አሀዝ እንዲወርድ ይደረጋል፡፡

አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገታችን 10.1 በመቶ እንዲሆን በትጋት ይሰራል ብለዋል፡፡

Share this Post