የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካነሷቸው ጥያቄዎች፡-
ኢትዮጵያ ያቀረበችው ፍትሐዊ የባህር በር ጥያቄ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
ከፍተኛ ድጎማ ተደርጎበት ወደ ሀገር ቤት የሚገባውን ነዳጅ በፍትሐዊነት ለማከፋፈል ምን እየተሰራ ነው?
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉትን የፀጥታ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ከኢትዮጵያውያን ምን አይነት ድጋፍ መደረግ አለበት?
መንግሥት ከአጋር አከላት ጋር በመተባበር በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች የቤት እጥረትን ለመቅረፍ ምን አዳዲስ ፖሊሲዎችና ዕቀዶች ተዘጋጅተዋል?
መንግሥት በጤናው ዘርፍ የሚታየው የመድሀኒት፣ የህክምና መሳሪያዎችና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ ምን አይነት ተጨባጭ ርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል?
የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጄክቶችን በተያዘላቸው ጊዜያት ለማጠናቀቅ ምን እየተሰራ ይገኛል?