የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (E-Mobility) ስትራቴጂና የትግበራ ማዕቀፍ በይፋ ተጀመረ

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ፣ መንግሥት ዘመናዊ፣ አረንጓዴና የኢኮኖሚ እድገትን የሚደግፍ የትራንስፖርት ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ልማት የካርቦን ልቀትን እና በነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሩ በተጨማሪም የኤሌክትሪፊኬሽን ሥራዎች በመላው የትራንስፖርት ሰንሰለት ውስጥ የተቀናጀ አሰራር እንዲኖራቸው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም የተሽከርካሪ እና የአገልግሎት ዕቅድ፣ ሎጂስቲክስ፣ የቻርጅ መሠረተ ልማት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፣ የደህንነትና የመመዘኛ ሥርዓቶች እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን እንደሚያካትት አስረድተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ክቡር መላኩ አለበል በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሥርዓትን እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

ስትራቴጂው የማምረቻ አካባቢ ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ኢንቨስትመንት እና የስራ ዕድል ፍጠራን እንደሚያበረታታ ተናግረዋል።

የተጀመረው ስትራቴጂ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ለማስፋፋትና የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን የተዘጋጀ ሲሆን፣ በውስጡም፦

የቻርጅ መሠረተ ልማት ማስፋፋት፣

የተቀናጀ የሎጂስቲክስና የትራንስፖርት ሥርዓት ማበረታታት፣

የኤሌክትሪክ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ማስፋፋት፣

የደህንነትና የመመዘኛ ሥርዓቶችን ማጠናከር፣

የኃይል አቅርቦትና የታዳሽ ኃይል ቅንጅት፣

የአቅም ግንባታና የተቋማት ቅንጅት፣

በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማምረትና አሰባሰብ ላይ ኢንቨስትመንት ማበረታታት፣

ንጹህ፣ ቀልጣፋና ለአካባቢ ተስማሚ የከተማ እንቅስቃሴን ማጎልበት ያካትታል።

ስትራቴጂው የኢትዮጵያን አረንጓዴ ኢኮኖሚ እድገትና የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ልማት ራዕይ ለማሳካት የሚያግዝ ሲሆን፣ ኢትዮጵያንም በአፍሪካ የኤሌክትሪክ መኪኖች ትግበራ ቀዳሚ ሀገር እንድትሆን ያግዛል።

በስትራቴጂው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ትስስር እና መሠረተ ልማት ልማት ዲቪዥን ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሊሲንጌ፣ ክቡራን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታዎች አቶ በርኦ ሀሰን እና አቶ ደንጌ ቦሩ፣ እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ተባባሪ ድርጅቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Ethiopia Launches National E-Mobility Strategy

Ethiopia has officially launched its National E-Mobility Strategy and Implementation Framework, marking a major step toward sustainable and climate-resilient transportation.

Speaking at the launch event, Minister of Transport and Logistics HE.Dr. Alemu Sime said Ethiopia is committed to building a modern, green, and resilient transport system through electric mobility.

He emphasized that electrification efforts must be coordinated across the entire transport chain, including logistics, charging infrastructure, energy readiness, safety standards, and stakeholder collaboration.

Minister of Industry HE. Melaku Alebel stated that the strategy will support Ethiopia’s industrial transformation by creating opportunities for local manufacturing, vehicle assembly, investment, technology transfer, and job creation.

The strategy focuses on expanding EV charging infrastructure, promoting electric public transport, strengthening regulatory systems, integrating renewable energy, and encouraging environmentally friendly urban mobility.

The initiative is expected to support Ethiopia’s green economic growth agenda and strengthen the country’s leadership in electric mobility development in Africa.

Dr. Robert Lisinge from ECA, the two State Ministers of Transport and Logistics, development partners, and representatives from universities attended the event.

The launch program of the strategy was attended by Dr. Robert Lisinge Directer of Technology,innovation ,connectivity and infrastructure development Decision (UNECA), State Ministers of Transport and Logistics H.E. Bero Hassan and H.E. Denge Boru, as well as sector stakeholders, partner organizations, universities, and other invited guests.

Share this Post